ወግ


አንድ ሱቅ 90% ዲስካውንት እንዳደረገ በተለያዩ ማስታወቂያዎች ላይ ያነበበው የከተማው ነዋሪ ሱቁ በር ላይ ወረፋ መያዝ የጀመረው ከእኩለ ለሊት ጀምሮ ነው ::
ጠዋት ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በር ላይ ሰልፍ ይዘው በሚጠባበቁበት ግዜ አንድ ደቃቃ ሰውዬ በሰልፈኞቹ መሀል እየተጋፋ ከሰልፉ ፊት ወዳሉት ሰዎች እንደደረሰ "ሂድ ወረፋህን ጠብቅ " ብለው ገፈታትረው ወደ ውሀላ ይወረውሩታል ::
እንደምንም ሚዛኑን ጠብቆ በድጋሚ ወደፊት ገስግሶ ሲመጣ "ሰውዬ ወረፋህን ጠብቅ ስትባል አትሰማም ?" ብለው በቦክስ እየተቀባበሉ ያላጉታል :: መሬት ወድቆ ትንሽ ከተንፈራፈረ ቦሀላ እንደምንም ብሎ ይነሳና በምሬት ይህን ተናገረ ::
"ወላሂ ..... ከዚህ በውሀላ አንድ ሰው ንክች ቢያደርገኝ እችን ሱቅ አልከፍታትም




ደስ የሚል ቀልድ ሰማሁ ....... 
    የሆኑ ቻይናዎች ንፋስ ስልክ በሚገኘው በዬሴፍ የመቃብር ስፍራ ያልፋሉ:: የመቃብሩን ስፋር ትልቅነት ከተመለከቱ በኋላ "ይህንን የሚያክል ቦታ ምነው ዝም ብላችሁ አስቀመጣችሁት ለምን ለኢንቬስተር አትሰጡትም" ብለው ይጠይቃሉ አብሯቸው ያለውን አበሻ:: አበሻውም መልሶ "አይ ይህ እኮ የመቃብር ስፍራ ነው" ይላቸዋል:: ቻይናዎቹም "እንዴ ለምን ትቀብራላችሁ ማቃጠል ነው እንጂ" ይላሉ:: አበሻው መልሱ "እኛ ሀገር በቁም ነው የምናቃጥለው አለ" አሉ::

No comments:

Post a Comment